✦ Verified product
ንጹር ፍቅር
EUR 3.75
Title
StreetLib Totem
Verified independent store
→
Autore: Demeke MekonnenEditore: Mekonnen DemekeLingua: AmaricoIsbn: 9789999097673Pubblicazione: 09/01/2023Categorie: FICTION / Generale FICTION PER GIOVANI ADULTI / Generale FICTIO
N / Cristiana / Generale Sinossi:“ንጹር ፍቅር” በዴሳ ከምትባል የምዕራብ ሐረርጌ ከተማ ተነስቶ እስከ ብራስል የዘለቀ፣ በሁለት በፍቅር የወደቁ ወጣቶች የፍቅር ህይወት ዙሪያ ያጠነጠነ ልብ ወለድ ታሪክ ነው። መጽሐፉ ስለፍቅር፣ ሀይማኖትና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሲያተኩር፣ ፈጣሪ አለ ወይም የለም ለሚሉት እሳቦቶች መከራከሪያ የሆኑ የተለያዩ ነጥቦችን ያነሳል። የባዮሎጂ መምህርና የሞሌኩላር ባዮሎጂ ተማሪ የሆነው ዳሪዮስ፣ ጠንካራ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቢሆንም በምድር ላይ ህይወት እንዴት ተጀመረ ለሚለው ጥያቄ ‘የአዝጋሚ ለውጥ ሂደት’ (evolution) እና ‘የአእምሮ አስተውሎት ውጤት’ (intelligent design) የሚሉት አመለካከቶች ይሞግቱታል። በፍቅር የወደቀላት መስከረም በዴሳ ጤና ጣቢያ ውስጥ የህክምና ላብራቶሪ ቴክኒሺያን ናት። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የወደደችውና የተቀበለችው ወንድ ዳርዮስ ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው የመስከረም የኋላ ታሪክ፣ ‘ከእሳት ያመለጠች ትንታግ’ አሰኝቷታል። የሕይወትን ፈተናዎች የምትጋፈጥባቸው ጥበባት፣ ለዳርዮስ የሚያስገርም ብቻ ሳይሆን፣ ሰው ሁሉ የፍቅርን ውበትና ምንጭ የሚያይበት ነው ብሎ ያምናል። ፍቅራቸው ገና እንቡጥ እያለ፣ የሚያራርቃቸው ነገር ተፈጠረ። በዚያ ላይ ዳርዮስ፣ እምነት ኋላ ቀር አስተሳሰብ እንደሆነ ከምታምን አንዲት ቤልጂየማዊት ወጣት ጋር የጀመረው ግንኙነት፣ ከሚሞግተው የአዝጋሚ ለውጥ መላምት ጋር ተዳምረው፣ ‘በርግጥ ፈጣሪ አለን?’ ለሚለው ጥያቄ ከመንፈሳዊ ነገሮች ሌላ፣ ተጨባጭ የሆኑ መልሶችን ይፈልጋል። መጽሐፉ በአብዛኛው እውነተኛ በሆኑ ክስተቶች ላይ ቢነሳም፣ በታሪኩ ላይ ያሉ ገጸ ባህሪያት በሙሉ ልብ የወለዳቸው ናቸው። Pagine 323 Formato [EU] Stampa bianco e nero - standard - 148x210 mm - Carta crema - Copertina opaca Peso 369 gr.